ፄዋ ባቢሎን ይብሉከ ሶበ
በጸሖሙ መከራ
በምድረ ነኪር አፅራዕነ ስባሔ
እስከ ሰቀልነ እንዚራ
ወአመ ሜጥኮሙ ክርስቶስ ምስለ
ዘሩባቤል መልአከ ሐራ
በክልኤ ዓመት እመንግሥተ
ዳርዮስ ዳራ
ሰብሑከ በመዝሙር ዘዐሥር
አውታራ
ትርጉም፦
የባቢሎን ምርኮኞቸ አሉኽ
በደረሰባቸው ጊዜ መከራ
ምስጋናን አቋረጥን በባዕድ
አገር እስከ መስቀል ደርሰን እንዚራ
በመለስካቸውም ጊዜ ክርስቶስ
ካለቃ ዘሩባቤል ጋራ
በኹለተኛ ዓመት መንግሥቱ
ለንጉሥ ዳርዮስ ዳራ
አመሰገኑኽ በበገና በባለዐሥር
አውታራ