tag:blogger.com,1999:blog-8541091360448880611.post8562829913134179933..comments2022-04-01T12:56:11.920-07:00Comments on መዝሙረ ዳዊት The (Ethiopic) Psalms: እግዚኦ ጸወነ ኮንከነ (ትርጕም 2)Anonymoushttp://www.blogger.com/profile/15565762582024379710noreply@blogger.comBlogger1125tag:blogger.com,1999:blog-8541091360448880611.post-46254205701809733182011-05-14T21:36:53.852-07:002011-05-14T21:36:53.852-07:00የትሩፋንን ነገር እያተትኹ፤ ያኛም ነገር ትዝ አለኝና እንዲህ የሚል ዐሳብ ወደቀ...የትሩፋንን ነገር እያተትኹ፤ ያኛም ነገር ትዝ አለኝና እንዲህ የሚል ዐሳብ ወደቀብኝ፦<br /><br />ኢትዮጵያም ከዘመናዊው ዓለም ለመጎዳኘት ብላ አምላኳን ትታ "የምናምኒዝም ተራሮችን" (እንደ ማርክሲዝም ወዘተ ያሉትን ማለቴ ነው)፣ እንዲሁም ምናምኒዝሞቹን እንደወለደች የምትታመነውን "የሳይንስ ምድር" በማምለኳ ("ሳይንሳዊ ምናምኒዝም" አይደል የሚባለው?)፤ በውስጧ ያሉ ልጆቿ "ኢትዮጵያ ውስጥ ሰው ኾኜ ከምፈጠር ምነው አሜሪካ ጅንስ ኾኜ በተሠራኹ" እስከማለት የሚደርሱ "ፂውዋን ዘበኅሊና" (በአካል ሳይወዱ በግድ እዚያው ቢኖሩም በኅሊና ግን ፈጽመው የተማረኩ) ሲኾኑባት፤ የቀሩትም በስደት ተበታትነው የስቃይ ኑሮ ሲገፉ ይኸው ሰባ ዓመት ሊሞላት ነው። <br /><br />ታዲያ ይኸ አስከፊ ኹናቴዋ እንዲቀየር ምናልባት ይኽ መዝሙር ለልጆቿ የሚያስተምረው ቊም ነገር ይኖር ይኾን?Anonymoushttps://www.blogger.com/profile/15565762582024379710noreply@blogger.com