በገነት አትክልት ነገር፦() ጣዕም፣ () ልማላሜ፣ () ጽጌ፣ () ሥን፣ () ፍሬ፣ () መዐዛ፣ () ቈጽል፣ ይገኛል። እንዲሁም በመዝሙረ-ዳዊት ነገር፦ () አፍቅሮ-ጸላዕት፣ () ትሕትና፣ () ሃይማኖት፣ () ተስፋ-መንግሥተ-ሰማያት፣ (፭) ተአምኖ-ኀጣውእ፣ () ስርየት፣ () ምጽዋት ይገኛል።

Wednesday, January 5, 2011

እንኳን ለ"በዓለ-ወሊዶታ ለድንግል ዐማኑኤልሃ" አደረሰን

በዚህ ደስ የሚለው ደግሞ ደጋግሞ ደስ ይበለው፤ የሚከፋው ካለ ግን የደስታ መንፈስ ያድለው፤ ማንም ይውደድ ማንም ይጥላ ታሣሥ ቀን የድንግልም በዓሏ ነው። እስኪ ይህንን እመቤታችን ማርያም የተናገረችው የወንጌል ቃል ልብ እንበለው፦ "እስመ-ገብረ ሊተይለ ዐቢያተ" (ደግ ነገር/ድንቅ ተአምር ሠርቶልኛልና)። ምን ማለት ነው?
ምን ተሠራ?
ሊዘከር የሚገባው ደግ ሥራ። አይደለምን?
ማን ሠራው?
ባለቤቱ፣ እግዚአብሔር። አይደለም እንዴ?
ለማን ሠራው?  
ድንግል ማርያም። አይደለም እንዴ?
እንዴታ፣ ነው እንጂ!
ስለኾነም በቅጥነተ-ልብ ለሚመለከት የጌታ መለዱ የድንግል መውለዷ  አንድ እና ያው ክሥተት ነው። ነውና፤ የመለዱ በዓል ያው የመውለዷ በዓል ነው። እናም ይህንን ምስጢር ለማሳየት ስንል፦ ግእዝ ላልጠገበ ጆሮ እንደሚሻክር እያወቅነው ብቻ ሳይኾን፤ የት ለመድረስ እንደሚቸኩል ባንረዳውም "ለብርሃነ-ልደቱ" ማለት እንኳ እንደሚረዝምበት/እንደሚንዛዛበት በምንገምተው ትውልድ ውስጥ እንዳለን ሳንስተው "እንኳን ለ'በዓለ-ወሊዶታ ለድንግል ዐማኑኤልሃ' አደረሰን" እንላለን። "እንኳን 'ድንግል ዐማኑኤልን መውለዷ ለሚታሰብበት በዓል' አደረሰን" ማለት ነው። 

በዚህም "ኦድ" እንመስል ይኾናል፤ ከቅዱሳት መጻሕፍት ቃል፣ ከአበው ዐሳብ ግን አንርቅም። "ናሁ ድንግል ትፀንስ ወትወልድ ወልደ"ን ያስታውሷል። ከዚህም ጋር "እም" አባ ጊዮርጊስ በዚህ ዐቢይ በዓል እንዲነበብ በወሰኑት ድርሰት መጨረሻ እንዲህ ብለው ነበር፦
ዘንተ መጽሐፈ አዘዘ [ጊዮርጊስ]
ከመ-ይትነበብ በዕለተ-ተዝካራ[ለማርያም]
አመ (ዕሥራ ወተሱዑ) ለታሣሥ
እንተ-ባቲ አስተርአየ ዕበየ-ክብራ
ወተሰብሐ ሥነ-ምግባራ
ለዓለመ-ዓለም። አሜን ወአሜን።
ይህም ማለት፦ 
[ጊዮርጊስ] ይህ መጽሐፍ፦
[የማርያም] የክብሯ ታላቅነት በታየባት
የምግባሯ ውበት/ብቃት
በተገለጠባት/ባንጸባረቀባት
[የመውለዷ] መታሰቢያ በሚኾንባት  ዕለት
በታሣሥ እንዲነበብ አዘዘ።
ለዘላለሙ። አሜን፣ አሜን።
ማለት ነው።

ቸር ዐውደ-ዓመት ያውለን። ለብርሃነ-ልደቱ በሰላም እንዳደረሰን፤ ለብርሃነ-ጥምቀቱ በደና ያድርሰን። አሜን።












2 comments:

  1. i think light of truth out of darkness is coming through you guys. i appreciate what you are doing. please update us about EOTC principles especially how, when, why we used to pray psalms. some peoples use it for various purposes and i myself trying to use in morning at home prayer. what aspects are there to use for different purpose?
    thanks.
    Deacon frew

    ReplyDelete
  2. can you please explain what these terms mean?

    (፫) ጽጌ፣ (፬) ሥን፣ (፯) ቈጽል፣ (፩) አፍቅሮ-ጸላዕት፣ (፬) ተስፋ-መንግሥተ-ሰማያት፣ (፭) ተአምኖ-ኀጣውእ፣ (፮) ስርየት፣ ( ፯) ምጽዋት
    thanks

    ReplyDelete