በገነት አትክልት ነገር፦() ጣዕም፣ () ልማላሜ፣ () ጽጌ፣ () ሥን፣ () ፍሬ፣ () መዐዛ፣ () ቈጽል፣ ይገኛል። እንዲሁም በመዝሙረ-ዳዊት ነገር፦ () አፍቅሮ-ጸላዕት፣ () ትሕትና፣ () ሃይማኖት፣ () ተስፋ-መንግሥተ-ሰማያት፣ (፭) ተአምኖ-ኀጣውእ፣ () ስርየት፣ () ምጽዋት ይገኛል።

Tuesday, December 28, 2010

አርእስት (titles/themes)

ሊቃውንቱ፦
"...የመጻሕፍትን ከላይ አርእስታቸውን ከታች ኅዳጋቸውን ሳይመለከቱ፣ ጥልቅ ምስጢራቸውን ሳይመረምሩ፣ ንባባቸውን ብቻ ይዤ እተረጕማለኹ ቢሉ፤ ባልታሰበ የክህደት ጕድጓድ ውስጥ ይጥላል።" ይላሉ።
አርእስትን በተመለከተ አንድ ምሳሌ ብንመለከት በገላትያ ምዕራፍ ፭ ከቁጥር ፲፮ ጀምሮ እስከ ፍጻሜው ያለውን እንዲህ ያኼዱታል፦
፲፮ እብለክሙ በመንፈስ ሑሩ፤ በፈቃደ-ነፍስ ኑሩ። ወፍትወተ-ሥጋክሙ ኢትግበሩ፤ በፈቃደ-ሥጋችኹ አትኑሩ።... ከዚህ [ከእነዚህ ኹለት አርእስት] በዃላ አሥራ ዐምስቱን ፈቃዳተ-ሥጋ ቆጥሮ አትሥሩ፤ ዘጠኙን ፈቃዳተ-ሥጋ ቆጥሮ ሥሩ ለማለት ያመጣል።
፲፯ እስመ-ሥጋኒ ይፈቱ ዘኢይፈቱ መንፈስ፤ ነፍስ ልትሠራው የማትወደውን ሥጋ ሊሠራው ይወዳልና፤ [ከላይ በርእሱ] "ፍትወተ-ሥጋክሙ ኢትግበሩ" ላለው። ወመንፈስኒ ይፈቱ ዘኢይፈቱ ሥጋ፤ ሥጋ ሊሠራው የማይወደውን ነፍስ ልትሠራው ትወዳለችና፤ [ከላይ በርእሱ]"በመንፈስ ሑሩ" ላለው።...
እዚህ ላይ ልብ ልንለው የሚገባው እንደአርእስት (theme) ኾነው የተነገሩት ኀይለ-ቃላት ቀጣዩን ንባብ ለመፍታት ቁልፍ መኾናቸውን ነው። በርግጥ በዚህ ምሳሌ ውስጥ አርእስቱ የደራሲው ቃል፣ የንባቡ አካላት ናቸው። እንደአርእስት የተጠቀማቸው ቅሉ ራሱ ደራሲው ነው።

የመዝሙረ-ዳዊት አርእስት ግን ለየት ይላሉ። የትርጓሜ ውጤትቁልፍም ናቸው እንጂ የደራሲው ቃል የንባቡ አካል አይደሉም። አገኛኘታቸው ከመጽሐፉ በአፍኣ ከኾኑ ታሪካዊ ማስረጃዎች፣ ወይም ከሌላ መጻሕፍት፣ አለዚያም ደግሞ ከመጽሐፉ ይዘት በመነሣት በተደረገ ዐተታ ሊኾን ይችላል። ሌላም መንገድ አለ። እንዲህም ስለኾነ አርእስቱ እንደየመተርጕማኑ እምነትና ትምህርት ተለያይተው ይታያሉ። ታዲያ በበኩላችን ቅዱሳት መጻሕፍትን ስናጠና ዘወትር ለራሳችን መምከር ያለብን ይህንን ነው፦ ምንም የሚያማልሉ የትርጓሜ ስልቶች--የአርእስት አደላደልን  (designation of titles/thematization) ጨምሮ--ቢያጋጥሙ፤ እኛ ግን “ማእከለ-ማኅበር ወእንግልጋ ስተይ ማየ እምቀሱትከ፤ ወእምነቅዐ-ዐዘቅትከ”  ያለውን በማስታወስ ጥንቃቄ ልናደርግ ያሻል። አንድ ጊዜ በስልቱ ወይም በአርእስቱ እጅ ከሰጡ በዃላ በምስጢር ይዘቱ ለመመለስ ይቸግራልና። ይህም በቅድሚያ የራስን ጠንቅቆ የማወቅና የመጠበቅን ሐላፊነት ማስገንዘብ እንጂ፤ ሌላ መንገድ ለማየት፣ ዐዲስ ዐሳብ ለመስማት በጭራሽ ያለመፍቀድ ጕዳይ አይደለም።

እዚህ ላይ ሳንገልጠው ልናልፍ የማንወደው ዐቢይ ነገር ቢኖር፦ ዛሬ በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያናችን ሊቃውንት ከግእዙ እንደተተረጎመ በተነገረን የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ የምናገኛቸው የመዝሙረ-ዳዊት አርእስት እውን ከግእዙ የተገኙ ናቸውን? የለም፤ አይደሉም። 

በጉባኤ የሚሰጠው ትምህርት የሚለው እንዲህ ነው፦ ለዳዊት “ሰባቱ ሀብታት ተሰጥተውታል… ሀብተ-መንግሥት፣ ሀብተ-ክህነት፣ ሀብተ-ይል፣ ሀብተ-መዊዕ፣ ሀብተ-በገና፣ ሀብተ-ፈውስ፣ ሀብተ-ትንቢት። …ትንቢት መቶ ሃምሳ መዝሙር መድረስ ነው። እንዲህ ግን ስለኾነ አርእስቱ አሥር ነው።” የአርእስቱን ዝርዝር በዚሁ ገጽ በስተግራ በኩል ያስቀመጥነው ሲኾን፤ ከዚህ ክታብ ጋራ አያይዘንም አቅርበናል (እንደተለመደው የክታቡን ርእስ ሲኮረኵሙ ያገኙታል)። አርእስቱ ፍጹም ከተለያዩ፤ በትርጓሜ ጊዜ እንዴት ያለ የምስጢር ልዩነት እንደሚኖር ወደፊት በምሳሌ እናያለን።

No comments:

Post a Comment