በገነት አትክልት ነገር፦() ጣዕም፣ () ልማላሜ፣ () ጽጌ፣ () ሥን፣ () ፍሬ፣ () መዐዛ፣ () ቈጽል፣ ይገኛል። እንዲሁም በመዝሙረ-ዳዊት ነገር፦ () አፍቅሮ-ጸላዕት፣ () ትሕትና፣ () ሃይማኖት፣ () ተስፋ-መንግሥተ-ሰማያት፣ (፭) ተአምኖ-ኀጣውእ፣ () ስርየት፣ () ምጽዋት ይገኛል።

Tuesday, December 28, 2010

አርእስት (titles/themes)

ሊቃውንቱ፦
"...የመጻሕፍትን ከላይ አርእስታቸውን ከታች ኅዳጋቸውን ሳይመለከቱ፣ ጥልቅ ምስጢራቸውን ሳይመረምሩ፣ ንባባቸውን ብቻ ይዤ እተረጕማለኹ ቢሉ፤ ባልታሰበ የክህደት ጕድጓድ ውስጥ ይጥላል።" ይላሉ።
አርእስትን በተመለከተ አንድ ምሳሌ ብንመለከት በገላትያ ምዕራፍ ፭ ከቁጥር ፲፮ ጀምሮ እስከ ፍጻሜው ያለውን እንዲህ ያኼዱታል፦

Monday, December 27, 2010

እግዚኦ ጸወነ ኮንከነ

ለዚህ ትምርት በተቃና ኹናቴ መቀጠል፤ እንዲሁም ላገራችን፣ ለወገናችን፣ ለዓለም ሕዝብ ኹሉ፣ ለግል ሕይወታችንም ጭምር፤ ከዚች ክታብ ጋራ ተያይዞ በምናገኘው መዝሙር እንጸልይ። መዝሙሩ፦ የክታቧን ርእስ ስትኮረኵሟት ይራገፍላችዃል (click on the title of this post and it will be downloaded to you)። ስንጸልይም ኑሯችንን በመዝሙሩ ከተገለጠው "ይለ-ጸሎት" ጋራ በማገናዘብ--ማለትም እኛን የመዝሙሩ፣ መዝሙሩን የእኛ ገንዘብ አድርጎ አዋሕዶ በመውሰድ--እንጸልይ። በተዋሕዶ።

ግእዝ ማንበብ የማንችል፤ ዐማርኛ መጽሐፍ ቅዱሳችንን በመጠቀም እንጸልየው። ለነገሩ፤ ግእዝ በምንማርበት ምክታብ እንደቀረቡት መልመጃዎች በምልክት የተዘጋጀ ስለኾነ፤ ደጋግመን ካጠናነው አነባበቡንም በጥቂት ጊዜ ልናውቅበት እንችላለን። የዚህን መዝሙር የምስጢር ጥልቀት ግን ትርጕሙን ስንጀምር የምናየው ይኾናል።

መዝሙር ዘዳዊት ሃሌ ሉያ

ኢትዮጵያውያን ሊቃውንት አንዱንም አንዱን መጽሐፍ ለመተርጎም ሲነሡ፤ የደራስያኑን የስማቸውን ትርጕም ከሕይወት ታሪካቸው ጋራ ባጭሩ በማብራራት ይጀምራሉ። ከዚያም እንዳስፈላጊነቱ የመጽሐፉን ይዘት ጠቅለል ባለ መልኩ ያስተዋውቃሉ። መጽሐፉ ከአሥራው መጻሕፍት አንዱ የኾነ እንደኾነ፤ ያ መጽሐፍ ሲነበብ ሲተረጎም ከሐዋርያት መድረሱን፤ ሐዋርያትም ፹፩ መጻሕፍት ለቀሌምንጦስ ሲየስረክቡ ያንን መጽሐፍ አንድ ብለው ቆጥረው እንዳስረከቡት ይጠቁማሉ። እንደየመጽሐፉም ጠባይ በየመቅድሙ የሚጨምሯቸው ሌሎች ቊምነገሮች አሉ። እየቀደም እናያቸዋለን።

ወደመዝሙረ-ዳዊት ስንመለስ፤ ሊቃውንቱ ከኹሉ አስቀድመው ዳዊት ማለት ምን ማለት እንደኾነ፤ ለመንግሥት እና ለትንቢት እንዴት እንደበቃ ከተረኩ በዃላ፤ የተሰጡትን ሀብታት ጠቁመው፤ መላው መዝሙራት የሚያተኩሩባቸውን የተወሰኑ አርእስት ይገልጣሉ። ከዚያም እንደማናቸውም ቅዱሳት መጻሕፍት ኹሉ የመዝሙረ-ዳዊት ረብ፣ ጥቅም--ማለትም የተጻፈበት ዋና ምክንያት--ለኛ ምክር፣ ተግሣፅ፣ ዕዝናት ሊኾን እንጂ ለከንቱ እንዳይደለ "ወኵሉ ዘተጽሕፈ ለተግሣፀ-ዚአነ ተጽሕፈ። ከመ-በትዕግሥትነ ወበተወክሎ መጻሕፍት ንርከብ ተስፋነ። እንዲል ሮሜ ፲፭፡ " በማለት የሐዋርያውን ቃል አስታውሰው ትርጓሜውን ያኼዳሉ።

Wednesday, December 8, 2010

ፍካሬ ዘጻድቃን ወዘኃጥኣን

  • የጻድቃንን እና የጥኣንን ግብር ለይቶ የሚናገር መጽሐፍ ይህ ነው።
  • አንድም ጻድቃንን በለውዝ በገውዝ፣ ጥኣንን በዕፅ ከንቱ መስሎ የተናገረው መጽሐፍ ይህ ነው።

የኢትዮጵያ ሊቃውንት ሦስት ዐበይት የትርጓሜ ዐይነቶችን ይጠቀማሉ፣ ያስተምራሉ፦ () ነጠላ፣ () አንድምታ እና () የምስጢር ትርጓሜ። ኹሉንም እንዳቅማችን በመጠኑ እንዳስሳለን። እየቀደም።