በገነት አትክልት ነገር፦() ጣዕም፣ () ልማላሜ፣ () ጽጌ፣ () ሥን፣ () ፍሬ፣ () መዐዛ፣ () ቈጽል፣ ይገኛል። እንዲሁም በመዝሙረ-ዳዊት ነገር፦ () አፍቅሮ-ጸላዕት፣ () ትሕትና፣ () ሃይማኖት፣ () ተስፋ-መንግሥተ-ሰማያት፣ (፭) ተአምኖ-ኀጣውእ፣ () ስርየት፣ () ምጽዋት ይገኛል።

Saturday, May 14, 2011

እግዚኦ ጸወነ ኮንከነ (ትርጕም 2)

እግዚኦ ጸወነ ኮንከነ። ዘእንበለ-ይቁም አድባር ወይትፈጠር ዓለም ወምድር፤ እምቅድመ-ዓለም ወእስከ-ለዓለም አንተ ክመ
እስመ-ለቅነ በመዐትከ፤ ወደንገጽነ በመቅሠፍትከ።
ወሤምከ ጢአተነ ቅድሜከ፤ ወዕሉምነሂ ውስተ-ብርሃነ-ገጽከ።
፲ ...እስመ-ለፈት የውሀት እምኔነ፤ ወተገሠጽነ።
ባለፈው ክታባችን ርእሱ ላይ ያተኮርንበት ምክንያት አኹን ግልጽ እንደሚኾን ተስፋ እናደርጋለን። በተለይ ከአንድ ሌላ ርእስ ጋራ አነጻጽረን ስናየው።  እንደሚከተለው፦ 

በውጭው ዓለም በመዝሙረ-ዳዊት ጥናት የተጠመዱ ምሁራን ከመዝሙረ-ዳዊት ዐልፎ ለመላው ቅዱሳት መጻሕፍት፤ ለሌሎች ሥነ-ጽሑፎችም ጭምር የሚጠቅም የትርጓሜ ስልት ፈጥረዋል። ከነዚህ ስልቶች በዋናነት የሚጠቀሰው "Formgeschichte/Formkritik = Form-historical/Form-critical" (የቅርፅ ታሪክ/ዐተታ) ወይም "Gattungsgeschichte/Gattungskritik = Type-historical/Type-critical" (የዐይነት ታሪክ/ዐተታ) የሚሉት ነው።  ከዚህ ስልት ጋር በተያያዘ የሚጠሩ ታላላቅ ስሞችን ለማስተዋወቅ ያኽል ጀርመናዊውን ኸርማን ጕንክልን እና ኖርዌያዊውን ዚግመንድ ሞቪንክልን መጥቀስ ይቻላል። ታዲያ በነዚህ ታላላቅ ምሁራን ላይ የተመሠረተው ጥናት የደረሰበት የመዝሙር ፹፱ ዐይነቱ (ፎርሙ፣ ታይፑ)፦ "community prayer song" (የማበር ጸሎት መዝሙር) የሚል ነው ( ሌሎችም ዐይነቶች  ይጠቀሳሉ፤ ለጊዜው እንለፋቸው)። በዚሁ ስልት መሠረት እንደተወሰነው፤ የመዝሙሩ ዐይነተኛ መልእክትም የሰውን ዐላፊ ጠፊነት እና የእግዜርን ዘለዓለማዊነት ማስተማር ነው። ማለፊያ አይደለም? ነው እንጂ፤ ልዩነት እና ጥልቀት (specificity and depth) ግን ይጎድለዋል።

ወደኛ ስንመጣስ? እንግዲህ ለኛ ዋናው ቊልፋችን "በእንተ-ትሩፋን" የሚለው ርእስ ነው ብለናል። መዝሙሩን በዚህ ርእስ ከፍተን ስንገባ ምን እናገኛለን? ማለትም፤ ከትሩፋን ጋር ያለውን ትይይዝ መገንዘባችን ከላይኛው ትርጕም የተለየ ምን ትርፍ ይሰጠናል? በትግሥት እንከታተል።

እስራኤልን ለምርኮ ያበቃቸው፤ ተራ ጥፋት፣ ጥቃቅን ጢአት አልነበረም። ለእስራኤል ምርኮ ለኢየሩሳሌም መጥፋት ዋና ምክንያቱ አምላካቸው እግዚአብሔርን መተዋቸው ይልቁንም አድባር አውግር ማምለካቸው ነበር። ይኸውም ለነቢዩ ኢሳይያስ አስቀድሞ ተገልጦለት በትንቢቱ የመጀመሪያ ምዕራፍ እንዲህ ብሎ ነበር፦

፩፡፬ እፎ ደግምዎ ለእግዚአብሔር።
(እግዚአብሔርን እንዴት ተዋችኹት? እንዴት ተዋችኹት? እንዴት ተዋችኹት?)

በዚህም ምክንያት እግዚአብሔር እንደሚቆጣ፣ መከራም እንደሚመጣባቸው በብዙ ቦታ፤ እዚያውም በቊጥር ነግሯቸዋል፦
 ኵሉ ርእስ ለሕማም። ወኵሉ ልብ ለዘን። (የሰው ኹሉ ራስ ለመገጠብ ይኾናል። [ተማርከው በሚኖሩበት] ትብትብ ምንጣፍ በመሸከም። አንድም...ንጉሡ ለመከራ፣ ሊቀ-ካህናቱ/ነቢዩ ለዘን ይኾናል። አንድም... ልዑላኑ ለመከራ፣ ዐዋቆቹ ለዘን ይኾናሉ።)
በምርኮው ጊዜ የነበረው ነቢይ ዳንኤልም እንዲህ ብሏል፦ 
፡፳፰- ...እስመ-በኵነኔ-ጽድቅከ አምጻእከ ዘ ኵሎ በእንተ-ጢአትነእስመ-አበስነ ወጌገይነ ደግናከ
(ስለ ጢአታችን ይኽን ኹሉ ፈርደኽ አምጥተኽብናልና፤ አንተን በሕግ በአምልኮት የተውንኽ እኛ ፈጽመን በድለናልና።)
ይልቁንም ስለኢየሩሳሌም መጥፋት እና ስለሕዝቧ መማረክ ልቅሶውን (ሰቆቃውን) ጭምር የጻፈልን ኤርምያስ እያተትነው ያለውን ነገር ቊልጭ አድርጎ ያሳየናል (ከምዕራፍ በረጅሙ እንጥቀስ)፦

ከመዝ ይቤ እግዚአብሔር፦
ምንተ ረከቡ አበዊክሙ ላዕሌየ በዘይግዕዙኒ ከመ-ይርሐቁ እምኔየ ነዋ? (ከኔ ፈጽመው ይርቁ ዘንድ፣ እኔን በሚነቅፉ ገንዘብ፣ እኔን የሚነቅፉበት አባቶቻችኹ በኔ ምን ተዋርዶ ምን ነቀፋ አገኙብኝ?)
ወሖሩ ወተለው ከንቶ (ኼደው ከንቱ ጣዖትን ተከተሉ፤ ከንቱ ጣዖትን አመለኩ።)
ወከንቶ ኮኑ። (እነሱም ከንቱ ኾኑ)...
ኪያየ ደጉኒ ነቅዐ-ማየ-ሕይወት (የሕይወት የረድኤት መገኛ እኔን በሕግ በአምልኮ ተውኝ)
ወከረዩ ሎሙ አዘቃተ ንጹፋተ ዘአልቦ ማይ። (እኔን ትተው ሕይወት ረድኤት የማይገኝበት ጣዖቱን አመለኩ)...
ናሁ ርእዪ ዘረሰየኪ ዲገ-ዚአየ። ይቤ እግዚአብሔር አምላክኪ። (ፈጣሪሽ እግዚአብሔር "እኔን መተውሽ ያደረገሽን ማድረግ እነሆ እዪ" አለሽ)
ተአምሪ ወትጠይቂ ከመ-ይመርረኪ ዲገ-ዚአየ ይቤ እግዚአብሔር አምላክኪ። ("እኔን በሕግ በአምልኮ መተውሽ መከራውን እንዲያመጣብሽ ዃላ ታውቂያለሽ ትረጅዋለሽ" አለሽ)...
ወትቤሊ ኢገበርኩ (አንቺ ግን ጢአት ሠርተሽ አልሠራኹም ትይኛለሽ።)
ዳዕሙ ተሐውሪ ውስተ-አድባር ነዋ (ጢአት ለመሥራት ጣዖት ለማምለክ ወደረጃጅሙ ተራራ ትኼጃለሽ። በተራራ ያመልካሉና፤ አንድም በተራራ የቆመውን ያመልካሉና...)
ወታሕተ-ኵሉ ዖም ዘቦ ጽላሎት (ጥላ ወዳለው ዛፍ ትኼጃለሽ)
ወበህየ ከዐውኪ ዝሙተኪ። (ከዚያውም ቦታ ዝሙትሽን አብዝተሽ ሠራሽው)...
እስመ-ልቈ-አህጉራቲከ አማልክቲከ ይሁዳ። ("ይሁዳ!" ብሎ ያሰማዋል፦ "የጣዖቶችኽ ቊጥር ባገሮችኽ ቊጥር ልክ ነውና")
ይህ እንዲህ ነው፤ በዚህም መሠረት በመዝሙር ፹፱ የምንሰማውን የ"ትሩፍ" ድምፅ ለመተርጎም እንሞክር።ትሩፍ በቊጥር ፦ "እስመ-ለፈት የውሀት እምኔነ፤ ወተገሠጽነ።"  ሲለን፤ "...ሕግ መጠበቅ (ሃይማኖት) ከኛ ጠፍቷልና፤ በመከራው ተገሠፅን" ማለቱ እንደኾነ እንረዳለን። በቊጥር እንደተገለጸው ደግሞ፦ "እኛ ጢአቱን፣ አምልኮተ-ጣዖቱን በየተራራው፣ በየኮረብታው ተሸሽገን ስንፈጽመው አንተ የማታይብን ቢመስለንም፤ አንተ ግን ታየን ኖሯል" ለማለት "ወሤምከ ጢአተነ ቅድሜከ፤ ወዕሉምነሂ ውስተ-ብርሃነ-ገጽከ።"  (ጢአታችንን በፊትኽ አኖርኽ፤ ማለት ታውቀዋለኽ። ተሸሽገን የሠራነው በደላችንም በፊትኽ ብርሃን ወለል ብሎ ይታያል፡) ይላል። [እዚህ ላይ ጽርኡን/ግሪኩን ተከትሎ የተሳሳተውን የግእዝ ንባብ በዕብራይስጡ ተመርጕዘን አርመነዋል፡ "ዓለም"ን "ዕሉም" ብለን።] እንዲህ ጢአታችን ወለል ብሎ በመታየቱ፣  አንተም በመቆጣትኽ  "...ለቅነ በመዐትከ፤ ወደንገጽነ በመቅሠፍትከ።" በመዐትኽ ተፈጸምን፤ በመቅሠፍትኽም ደነገጥን (ኢየሩሳሌም ጠፋች፣ እኛም ተማረክን)።...

ልብ እንበል፤ በመዝሙሩ ውስጥ ድምፁን የምንሰማው "ትሩፍ" የዚህ ታሪክ ባለቤት የነበረ "ተነሳሒ" እስራኤላዊ ነው (በነጠላም ይኹን በብዙ ምስጢሩ አይቀየርም)። ንስሐውም በደሉን ሲፈጽም አለማስተዋሉን በመገንዘብ፣ አኹን ግን ልብ ማድረጉን በማሳየት ሊኾን ይገባዋልና፤ መዝሙሩን ሲጀምር ቅሉ እንዲህ ብሎ ነው የጀመረው፦ "እግዚኦ ጸወነ ኮንከነ" እንዲያው የመታለል ነገር ኾኖ እንጂ፤ ዱሮውንም'ኮ ከትውልድ እስከትውልድ አምባ መፀጊያችን አንተው ነበርኽ። "ዘእንበለ-ይቁም አድባር ወይትፈጠር ዓለም ወምድር፤ እምቅድመ-ዓለም ወእስከ-ለዓለም አንተ ክመ" ወይ ሞኝነታችን፣ ወይ አበሳችን፣ ወይ በደላችን!፦ እሊያ አንተን ትተን ልናመልካቸው የሞከርናቸው አድባር-አውግሩ፣ መጥፎ ግብራቸውን በተከተልንላቸው በአሕዛብ ዘንድ አድባሩን አውግሩን እንደወለደች ትታመን እና የሕይወት እናት ተብላም ትመለክ የነበረችው ምድርም፣  ዓለም ቅሉ በሞላው እንጂ (!) ሳይፈጠሩ፤ ከኹሉ አስቀድሞ የነበርኽ፤ ዓለምንም አሳልፈኽ የምትኖር አንተ ነኽ 'ኮ! አንተ ነኽና... (እጅግ የተመቸ የትርጕም አግጣጫ አልያዝንም?)
እዚህ ይቆየን፤ እንቀጥላለን...
1 comment:

  1. የትሩፋንን ነገር እያተትኹ፤ ያኛም ነገር ትዝ አለኝና እንዲህ የሚል ዐሳብ ወደቀብኝ፦

    ኢትዮጵያም ከዘመናዊው ዓለም ለመጎዳኘት ብላ አምላኳን ትታ "የምናምኒዝም ተራሮችን" (እንደ ማርክሲዝም ወዘተ ያሉትን ማለቴ ነው)፣ እንዲሁም ምናምኒዝሞቹን እንደወለደች የምትታመነውን "የሳይንስ ምድር" በማምለኳ ("ሳይንሳዊ ምናምኒዝም" አይደል የሚባለው?)፤ በውስጧ ያሉ ልጆቿ "ኢትዮጵያ ውስጥ ሰው ኾኜ ከምፈጠር ምነው አሜሪካ ጅንስ ኾኜ በተሠራኹ" እስከማለት የሚደርሱ "ፂውዋን ዘበኅሊና" (በአካል ሳይወዱ በግድ እዚያው ቢኖሩም በኅሊና ግን ፈጽመው የተማረኩ) ሲኾኑባት፤ የቀሩትም በስደት ተበታትነው የስቃይ ኑሮ ሲገፉ ይኸው ሰባ ዓመት ሊሞላት ነው።

    ታዲያ ይኸ አስከፊ ኹናቴዋ እንዲቀየር ምናልባት ይኽ መዝሙር ለልጆቿ የሚያስተምረው ቊም ነገር ይኖር ይኾን?

    ReplyDelete